2merkato.com (Nov 18, 2026)
ቀን፡09/03/2019
የሳራ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ሰሜን ሸዋ፣ ጣርማበር፣ ሳራ አምባ
የፍላጎት መግለጫ ጥሪ (REQUEST FOR EXPRESSIONS OF INTEREST)
የሳራ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን/ገዳም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በሳራ አምባ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ጣርማበር ወረዳ ከ አዲስ አበባ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በገዳሟ ቅጥር ግቢ ውስጥ የቤተ ክርስቲያኗን የጣራ እድሳት ሥራ ፕሮጀክት ለማከናወን፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በቂ የቴክኒካል ብቃት ያላቸውን የሕንፃ ወይም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች (BC/GC) የፍላጎት መግለጫ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
1. የፕሮጀክቱ አጠቃላይ መግለጫ
|
የፕሮጀክቱ ስም
|
የሥራው ዓይነት
|
የሚፈለገው የተቋራጭ ደረጃ
|
የፕሮጀክቱ ቦታ
|
|
የሳራ አምባ ደብረ ገነት
ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
ቤተክርስቲያን የጣራ እድሳት
|
የጣራ እድሳት እና ተዛማጅ
የብረት ትረስ (Truss) ግንባታ ሥራዎች
|
BC/GC ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ
|
በሰሜን ሸዋ ዞን ፣
ጣርማበር ወረዳ ከ አዲስ
አበባ 200 ኪ.ሜ ርቀት
ላይ
|
2. የብቁነት መስፈርቶች (አስገዳጅ ሰነዶች)
- ፍላጎት ያላቸው ሥራ ተቋራጮች የፍላጎት መግለጫና የሚከተሉትን ወቅታዊ ሰነዶች አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፦
-
የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡ ለ2019 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ።
-
የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፡ በBC/GC-5 እና ከዚያ በላይ ደረጃ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ሰርተፍኬት።
-
የግብር ምዝገባ ሰነዶች፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)።
-
የሥራ ልምድ፡ ከዚህ በፊት ተሳትፈው በዋና ተቋራጭነት 100% የተጠናቀቁ ወይም ከ 70% በላይ የተገባደደ ፕሮጀክት የምስክር ወረቀት(ማስረጃ)።
ማሳሰቢያ፦
- የፍላጎት መግለጫዎች ከታች በተገለጸው አድራሻ እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት ወይም በዚያው ሰዓት መድረስ አለባቸው። ዘግይተው የሚደርሱ መግለጫዎች ተቀባይነት አያገኙም ።
- ኢሜይል፡ lawe.partners@gmail.com
- ቴሌግራም፡ @HR_ENGM
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ መረጃ ወይም ጥያቄ ካለዎት፣ ከላይ በተገለጸው አድራሻ በፅሁፍ ይላኩልን።