በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የመስተንግዶ፣ የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የመስተንግዶ፣ የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 19, 2026)

የግልፅ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ የጨረታ

መለያ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም

  1. የደንብ ልብስ
  2. አላቂ የፅዳት እቃዎች
  3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ
  4. የኤልክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች
  5. የህዝብ ትራንስፖርት
  6. የመስተንግዶ
  7. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ፍቃድ ያላችው እና ሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጭራቶች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚች።

2. የቅራቢነትን ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ ማቅረብ የሚችል።

ለሎቶች የተቀመጠው በኢትዮጵያ ብር

  1. ሎት 1 ደንብ ልብስ 20000
  2. ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች 12000
  3. ሎት 3 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 13000
  4. ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች 20000
  5. ሎት 5 የህዝብ ትራንስፖርት 2000
  6. ሎት 6 መስተንግዶ 2000
  7. ሎት 7 . የህትመት ውጤቶች 1200

5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በተቋሙ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ጨረታው እስከ 1ዐኛው ቀን 11፡30 ተሽጦ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ መቅረብ የማይችሉትን ቋሚ እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው ናሙና መሰረት በአካል ማሳየት የግዴታ ነው።

10.ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ እና ውል በተሰጣቸው 5 ቀን ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ለጽ/ቤቱ ማስረከብ አለበት።

11. መ/ቤቱ ጨረታ ሰነድ ላይ ካቀረበው እቃ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

አድራሻ፡–ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ገርጅ ናይጀሪያ ኢንባሲ አፖርትመንት አጠገብ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም ገርጅ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011 639 5582

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት