Addis Zemen (Nov 19, 2026)
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ውኃ ሥራዎች ኮርፓሬሸን ዋናው መ/ቤት ለአሽከርካሪዎች ማሰለጠኛ ማዕከል እና ለፕላስቲክ ስቶር አገልግሎት የሚጣሉ የደህንነት ካሜራ አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 07/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር ዓይነት Summery of goods |
መለኪያ
|
ብዛት |
ምርመራ
|
|
1 |
የደህንነት ካሜራ |
በቁጥር |
6 |
በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት |
- የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ መሆን አለበት። ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸዉን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ የሚሆን ለ90 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ብር 40,000.00 አርባ ሺህ ብር በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒ ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ስም ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ነጋ ቦንገር ሆቴል ጀርባ በመሄድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማስገባት እና በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20/ሃያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዱን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ በዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 በ20ኛው ቀን በ8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ካላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውኃ ሥራዎች ኮርፓሬሽን በዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ
የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት
ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከመሰናዶ ትምህርት ቤት ጎን
ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ፖ.ሣ.ቁ 106
ስልክ ቁጥር 058 222 147
ባህር ዳር፡
ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን