Addis Zemen (Nov 19, 2026)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር/ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ስራዎች
- ሎት 1 የአማን ጤና አጠባበበቅ ጣቢያ ግንባታ
- ሎት 2፡– የአማን ቁጥር 1 ቅድመ መደበኛ ሞዴል ት/ቤት ግንባታ
ግንባታ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC/BC/ የሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተቋራጮች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ከግዥ ንብ/አስር የሥራ ሃደት ቢሮ 2,000 ሁለት ሺ ብር ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን : ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 300,000 ሶስት መቶ ሺ ብር ለሎት ሁለት 100,000/አንድ መቶ ሺ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ አ ከ አስር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ22ኛው ቀን ሎት አንድ ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ሠዓት፣ ሎት ሁለት 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት