የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ የዩቪፕሪንት ክችን ካቢኔት፤ የመሰብሰቢያ ጠረጴዛ፤ የግድግዳ ማስዋቢያ አቅርቦትና ገጠማ ስራ እና የስብሰባ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ የዩቪፕሪንት ክችን ካቢኔት፤ የመሰብሰቢያ ጠረጴዛ፤ የግድግዳ ማስዋቢያ አቅርቦትና ገጠማ ስራ እና የስብሰባ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ-018/2019

ተቋማችን ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ የዩቪፕሪንት ክችን ካቢኔት፤ የመሰብሰቢያ ጠረጴዛ፤ የግድግዳ ማስዋቢያ አቅርቦትና ገጠማ ስራ እና የስብሰባ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የዩቪፕሪንት ክችን ካቢኔት፤ የመሰብሰቢያ ጠረጴዛ፤ የግድግዳ ማስዋቢያ አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግዥ

45,000.00

ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

2

የስብሰባ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም  አቅርቦትና ገጠማ ስራ ግዥ

50,000.00

ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. አድራሻ፡– ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር 011-156-01-48

3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <<ETHOPIAN ELECTRIC UTILITY>> በሚል መሆን ይኖርበታል፤

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

6. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *