ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ለ PROJECT ZERO አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች (መደብ 1) እና ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ አላቂ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች (መደብ 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ለ PROJECT ZERO አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች (መደብ 1) እና ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ አላቂ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች (መደብ 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዞን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተገለፁት ሁለት የጨረታ መደቦች ለመሳተፍ ፍላጎት ያለቸውን ድርጅቶች በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡-

  1. አይነተኛ የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አካል ለሆነው የ PROJECT ZERO አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዢ ጨረታ……የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400..00/አራት መቶ ብር/፤
  2. ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ አላቂ መድኃኒቶች እና የሕክምና መገለገያዎች ግዢ ጨረታ——- የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300..00/ሦስት መቶ ብር/፤

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በ ቱመርካቶ ድረ-ገፅ/2merkato.com/ https://tender.2merkato.com/  ላይ ከወጣበት ኅዳር 11፣ 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስራ-አንድ/11/ ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል የፋይናንስ ክፍል በመቅረብ በየመደቦቹ አንፃር የተገለፀውን የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ በመክፈል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተወዳዳሪዎች ዌንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማክሰኞ ኅዳር 22፣ 2019ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዐት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በአንዱ ወይንም በሁለቱም የጨረታ መደቦች መሣተፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ለሁለቱም መደቦች የሚሳተፉ ድርጅቶች መወዳደሪያቸውን ለይተው ማቅረብ አስገዳጅነት ይኖረዋል፡፡ የጨረታ መደቡን ሳያመለክቱ ወይንም ሳይለዩ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መወዳደሪያቸው ውድቅ ይደረጋል፡፡

ሁለቱንም የጨረታ መደቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ E-mail: enquiries@hamlinfistula.org 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *