Addis Zemen (Nov 20, 2026)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 004/2019
በአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅታችን ከነማ ፋርማሲ የጅማላ ንግድ አከፋፋይ አገልግሎት የመድሀኒት እና የህክምና መገልገያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የሀገር ውስጥ የመድሀኒት አምራች እና የመድሀኒት አስመጪ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች፡–
1. በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ምዝገባ ፍቃድ ያለው።
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና የቫት ሰርተፊኬት።
3. EFDA ሰርተፊኬት፣ GMP ሰርተፊኬት፣ product registration ሰርተፊኬት፣ ማርኬት አውተራይዜሽ፣ ፕሮዳክት ሪጅስትሬሽን።
4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ/ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም። በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ በዋለበት ቀን በዋናው መ/ቤት ማስታወቂያ ቦርድ እንዲሁም በተለያዩ የበይነመረብ አማራጮች በምናሳውቀው ቀንና ሰዓት መሰረት ከተጫራቾች ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የቅድመ–ጨረታ ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑን እንገልፃለን።
- አድራሻ፡– ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ/ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
- የስራ ሰዓት፡– ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 172-7137
በአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት