የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ ለከባድ ማሽነሪና ቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሆን ልዩ ልዩ ዘይትና ቅባት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ ለከባድ ማሽነሪና ቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሆን ልዩ ልዩ ዘይትና ቅባት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዘይ/ቅ-1- /2019

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ ለከባድ ማሽነሪና ቀላል ተሽክርካሪዎች አገልግሎት የሚሆን ልዩ ልዩ ዘይትና ቅባት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በመሆኑም

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2.  ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ 1፣ ኮፒ 2 በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሽናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀን 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘንድ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅደመ ሁኔታዎቸ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲ ፒ ኦ /c.p.0/ ብር 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ “ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። እንዲሁም ጨረታወን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ይወረሳል ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
  8. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት::
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

የስልክ ቁጥር 0113659932

ወልቂጤ– ኢትዮጵያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *