የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዋና ሕንፃው ውስጥ የሚገኙ የስብሰባ አዳራሾች (Interior Design, Furnished and Fit-Out of Meeting Halls Furnishing and Renovation Works) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዋና ሕንፃው ውስጥ የሚገኙ የስብሰባ አዳራሾች (Interior Design, Furnished and Fit-Out of Meeting Halls Furnishing and Renovation Works) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 14/2019

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዋና ህንፃ ውስጥ የሚገኙትን የስብሰባ መሰብሰቢያ አዳራሾች Interior Design, furnished and Fit-Out of Meeting Halls Furnishing and Renovation Works ለኮንስትራክሽን ስራዎች የሚውል በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች የዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (VAT)፣የግብር ከፋይነት ሠርተፍኬት (TIN)፣የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ስለ ግብር አከፋፈል የተሰጠ ማስረጃ ሠነዶች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. በተቁ 1 ከተጠቀሱት በተጨማሪ ተጫራቾች ደረጃቸውን የሚገልጽ የታደሰ የምስክር ወረቀት፣ከሚመለከተው አካል/ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፣ ለሥራው የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና እቃዎች ዝርዝር መግለጫ፣ ለሥራው  የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች መግለጫ ዝርዝር እና በጨረታው ለተጠየቀው ሥራ ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ለስራው አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ 09/04/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በዚሁ ቀን 09/04/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዋ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።

6. ተጫራች የሥራውን ዓይነትና ሁኔታ በአካል በመገኘት ማየትና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ።

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

አድራሻ:- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣርቤት በሚወስደው

መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር 011-551-3288

ፖ.ሣ.ቁ 3375 አ.አ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *