በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 21, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣

በዚሁ መሠረት፣

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ምርመራ

1

ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር

በቁጥር

10

ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጉ በዕለቱ በ8፡30 ይከፈታል።

በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዝርዝር መረጃውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ

በመሆኑም ተጫራቾች

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በክልሉ ጤና ቢሮ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋና ዶክመንታቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል። ጨረታ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።

7. ጨረታው በቢሮው ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል።

9. አሸናፊው ድርጅት የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ውል የሚፈፀም ሲሆን ያሸነፈውን ዕቃ ንብረት ክልል ጤና ቢሮ ወራቤ ማቅረብ ይጠበቅቦታል።

10. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙለም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ 09 11 83 24 63 / 16 86 97 50

የማ/ኢትዮጵያ/ ክ/መ/ጤና ቢሮ

ወራቤ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *