የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 21, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር A/S/C/P/D 02/2019

የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት– 1

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

10,000.00

ሎት 2

የደንብ አልባሳት

5,000.00

  • የታደሰ የዘመኑን የንግድ ፍቃድ ያለውና በጨረታ ተሳታፊ ለመሆን ከግዥ ኤጀንሲ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ የሆነ
  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የሚገልፅ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
  • የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ነው፤ ሰነዱ የሚሸጠው በየሎቱ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ነው፤ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብቻ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማያያዝ እና የቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  • የሚቀርቡ ዋጋዎች በሙሉ ቫት አካቶ መሰራት አለበት።
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በክፍለ ከተማው ቢሮ ቁጥር 26 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ “ማስገባት ይችላሉ።
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን 4.00 ተዘግቶ 4.30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በመ/ቤቱ መመዘኛ መስፈርት / specification/ ባወጣንባቸው ዕቃዎች ላይ ሌላ የራስን /spec/ አውጥቶ መወዳደር አይቻልም።
  • የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ከስራ ቀናት ውጪ እና የክብረ በአል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል። ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  • አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን ውል ከተዋዋለበት ጊዜ/ጀምሮ ያሸነፈበትን ዕቃ ማስገባት አለበት።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • የጨረታው አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና መስጠት ይኖርበታል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፒያሳ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፊት ለፊት የአዲስ አበባ ውኃ እና ፍሳሽ አራዳ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ሲሆን ቢሮ ቀጥር 26 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 157 4264 / 011 126 7187/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *