የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለመፈጸም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት

  • ሎት-1 የደንብ ልብስ ሎት 2 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሎት 3 የዕዳት ዕቃዎች ሎት 4 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-5 ቋሚ ዕቃዎች እንዲሁም 6 የህንፃ ጥገና 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስጠገን ይፈልጋል።

 በዚሁ መሰረት ተጫራቾች

1. የመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያለው፣

2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።

3. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይቻላል።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

7. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የእቃው ከታች በየሎቱ የተዘረዘረውን ብር በጥሬ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ሲፒኦ((CPO)ተጫራቾች ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊው ያስያዙትን ወዲያውኑ ይመለሳል።

8. ጨረታውን ለማባዛት መሞከር ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ጨረታ ማስከበሪያም እንደሚወረሱ ማወቅ አለባቸው።

9. ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ11ኛ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን በ4፡ 30 ሰዓት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ ቀን በሰዓቱ ይከፈታል።

10. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገደ መሆን ይኖርበታል።

12. እስፔስፊኬሽን ላልቀረበላቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርብ ዋናውንና ቅጂውን በሚመስከተው መፈረምና ማህተም መደረግ አለበት።

14. በዋጋ መሙያው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ተቀባይነት የለውም።

15. ጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን ዓይነት ምርት እደሚያመርቱ እና ብቃት ማረጋገጫ ምስክረ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡ ፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ጅምላ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስረከቢያ : የውል ማስረከቢያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።

16. ውል የገባው ተጫራች ውሉን በገባበት ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ካላስገባ በየቀኑ የሚታሰብ ውል በገባበት ሂሳብ ልክ 1 ፐርሰንት (%) የሚታሰብ ቅጣት አለው:: ለሎት- 1 ብር 25,000፣ ለሎት2 ብር 15,000፣ ለሎት-3 ብር 18,000፣ ለሎት- 4 ብር 15,000፣ ለሎት-5 ብር 25,000፣ ለሕንፃ ጥገና -6 ብር 17,000፣ ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና -7 ብር 15,000 ተጫራቾች ማስያዝ ደኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ:- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በ2 ፖስታ አሽጋችሁ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች በኦርጂናል እና በኮፒው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ሊያቀርቡ ይገባል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 ይሆናል እንዲሁም ናሙና መረከቢያ ጊዜ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት እስከ 400 ይሆናል፡፡ አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አንዶዴ የመ/ደ/ት/ቤት ቴሌ ግምጃ ቤት ባለው መንገድ ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ 011- 435- 20 69/70
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት