Addis Zemen (Nov 21, 2026)
የኮንክሪት ሚክስ የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናውነው አስቸኳይ ፕሮጅክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንክሬት ሚክስ ምርት በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የምርቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የአንድ ሜ.ኪ ነጠላ ዋጋ+ ትራንስፖርት + ተ.እ.ታ ጨምሮ |
|
1 |
Concrete C-25 Without Pump |
ሜ.ኩ |
25,141 |
22,099.70 |
|
2 |
Concrete C-30 Without Pump |
ሜ.ኩ |
6,949 |
23,114.00 |
1. አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ–ገጽ ላይ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
2. የኮንክሪት ሚክስ ማምረቻ ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ህጋዊ ውክልና፤በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የኮንክሪት ሚክስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ፣ ወይም ኮንክሪት ሚክስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ/ ማህበር የተሰጠ ህጋዊ/በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት የተረጋገጠ/ ውክልና አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቹ ለእያንዳንዱ የኮንክሪት ምርት አይነት በቀን ቢያንስ 40 ሜ.ኪ ወይም ከሶስትም የምርት አይነቶች በድምሩ ቢያንስ በቀን 120 ሜ.ኩ እና ከዚያ በላይ ምርት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
4. የሚቀርበው ምርት በባለስልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /specification/ መሰረትመሆኑ መ/ቤቱ የላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናወናል።
5. አቅራቢው የኮንክሪት አይነቶች ሚክስ ዲዛይን ዶክመንት፤የኮንከሪት ጠጠር እና አሸዋ የጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ግዜ ውስጥ ፍቃድ ካለው የላብራቶሪ ማዕከል ወይም ተጫራቹ በራሱ ላብራቶሪ የተከናወነ ሆኖ ህጋዊ ስልጣን ባለው ተቋም/ አማካሪ የተረጋገጠ ዶክመንት ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
6. አቅራቢው ውል በተዋዋለ በ1 ቀን ውስጥ አቅርቦት መጀመር አለበት።
7. ተጫራቾች ኮንክሪት ማምረቻ ማሽኑን በሚመለከት የማሸኑን የማምረት አቅም የሚገልፅ ቴክኒካል ሰነድ /ሊብሬ/ማቅረብ አለበት የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንቱ ዝቅተኛ የማምረት አቅሙ 30m3 /Hr መሆኑ አለበት ማረጋገጫ በፅሁፍ ማቅረብ አለባቸው።
8. በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከ15% በላይ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ኮንክሪት ሚክስ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ወጪ ላይ ብቻ ከ7ሜ.ኩ እስከ 10 ሜ.ኩ በሚጭኑ የትራክ ሚክሰሮችን ለ1 ኪ.ሜትር ደርሶ መልስ 1.18 ሊትር የነዳጅ ፍጆታ ተመን መሰረት ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል።
9. አቅራቢዎች ለምዝገባ በሚቀርቡበት ቅደም ተከተል መሰረት የመ/ቤቱ ፍላጎት እስኪሟላ ድረስ ይስተናገዳሉ።
10. ባለስልጣን መ/ቤቱ ከ5-10 በመቶ ቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ለሚያቀርቡ አቅራቢዎች ብቻ ይከፍላል።
11. አቅራቢዎች ውል ለተዋዋሉበት የውል መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ከታወቀ ባንክ የክፍያ መዘዣ ወይም በሁኔታላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-25 / 011-3-71-41-03
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን