Addis Zemen (Nov 21, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የንግድና የቢሮ ሕንፃ ገበያና እዋጭነት ጥናት አገልግሎት ግዥ የድርጅቱ ስም፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ድርጅታችን ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ቢሆንም፣ የድርጅቱን የፋይናንስ ዘላቂነት ለማጠናከርና ተቋማዊ ተልዕኮውን በቀጣይነት ለማስፈጸም የሚያስችል የገቢ ምንጭ ለማልማት ያቀደ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በሚገኘው የድርጅቱ ይዞታ ላይ የንግድና የቢሮ ሕንፃ ለማንባት አቅዷል።
ስለሆነም የታቀደው ፕሮጀክት የገበያ ፍላጎት፣ የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ አዋጭነት ለመገምገም፣ ተገቢውን የልማት አማራጭ ለመለየትና ለትግበራ የሚያግዝ ዝርዝር ጥናት ለማሰራት በዘርፉ ብቃትና ልምድ ያላቸውን የአማካሪ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።
1. የጥናቱ ዓላማ፡–
የጥናቱ ዋና ዓላማ በድርጅቱ ይዞታ ላይ የሚገነባው የንግድና የቢሮ ሕንፃ የገበያ፣ የቴክኒክና የፋይናንስ አዋጭነት መገምገም እና ለድርጅቱ ዘላቂ የገቢ ምንጭ የሚሆን ተገቢ የልማት አማራጭ ማቅረብ ነው።
2. የጥናቱ የሥራ ወሰን (Scope of Work)
ተመራጩ አማካሪ ድርጅት ቢያንስ የሚከተሉትን ሥራዎች ማከናወን ይጠበቅበታል።
- የገበያ ጥናት (Market Study) በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 2 የሚገኘው በአካባቢው የንግድና የቢሮ ቦታ ፍላጎት፣ የኪራይ ዋጋ፣ የተፎካካሪ ሕንፃዎችና የደንበኞች ፍላጎት መተንተን።
- የቴክኒክ ጥናት (Technical Feasibility) የመሬቱን ሁኔታ፣ የሕንፃ አቀማመጥ፣ የወለል ብዛት፣ የግንባታ ስፋትና የአጠቃቀም አማራጮችን መገምገም።
- የፋይናንስ አዋጭነት (Financial Feasibility) የግንባታ ወጪ፣ የሥራ ማስኬጃ ወጪ፣ የኪራይ ገቢና የተጣራ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ ማዘጋጀት።
- የኢኮኖሚ ትንተና ፕሮጀክቱ ለድርጅቱ የሚያስገኘውን የገቢ እድልና የፋይናንስ ዘላቂነት መግምግም።
- የአደጋ ትንተና : የግንባታ ወጪ ጭማሪ፣ የገበያ ለውጥ፣ የኪራይ ፍላጎትና የባዶ ቦታ መጠን ተፅዕኖ መተንተን።
- የአማራጮች ንጽጽር የተለያዩ የሕንፃ ዲዛይንና የአጠቃቀም አማራጮችን በወጪ፣ በገቢና በትርፋማነት ማነፃፀር።
- የትግበራ ዕቅድ የፕሮጀክቱን የግንባታስ ደረጃዎች የጊዜ ሰሌዳ፣ የፋይናንስ ስፍላጎትና የትግበራ ስትራቴጂ ማቅረብ።
3. የሚቀርቡ የጥናት ውጤቶች (Deliverables)
- የገበያ ጥናት ሪፖርት።
- የቴክኒከ አዋጭነት ጥናት።
- የግንባታ ወጪ ግምት፡
- የፋይናንስ ሞዴልና የገቢ ትንበያ።
- የNPV፣ IRR፣ Payback Period እና Sensitivity Analysis ውጤቶች።
- የተመራጭ የፕሮጀክት አማራጭ ምክረ ሀሳብ
- የመጨረሻ ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት፡
4, የተጫራቾች ብቃትና መስፈርቶች፡–
- በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው መሆን።
- በገበያና አዋጭነት ጥናት የተለየ ልምድ ያለው መሆን።
- በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በአርክቴክቸርና በሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ማቅረብ።
- ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን የሠሩበትን ማስረጃ ማቅረብ።
5. የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ።
- TN እና የግብር ክሊራንስ።
- የድርጅቱ መግቢያና የሥራ ልምድ መግለጫ።
- የቴክኒክ ሀሳብ (Technical Proposal)።
- የፋይናንስ ሀሳብ (Financial Proposal)።
- የባለሙያዎች CV እና የትምህርት ማስረጃዎች።
- የቀድሞ ተመሳሳይ ሥራዎች ማስረጃ።
- የጨረታ ማቅረቢያና መክፈቻ
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉና ስራውን የምትሰሩበት የአገልግሎት ዋጋ በመግለፅ መረጃችሁን የቴክኒከና የፋይናንስ ሰነዶች በተለያዩ በስማቹ በታሸገ ኢንቨሎፕ አያይዛችሁ በጨረታ እንድትወዳደሩ እንጠይቃለን።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 ብር /አምስት ሺ ብር/ በሲፒኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነድ በብር 500.00/ብር አምስት መቶ/ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው የሚቆየው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት የስራ ቀናት ሲሆን የሚከፈተው በማግስቱ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ወኪል) በተገኙበት ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሰነድ ማቅረቢያ ቦታ፦ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 521 መስቀል አደባባይ ኢግዚቢሽን ማእከል ጀርባ
ስልክ ቁጥር፡– 0115576162 / 0911440933 / 0985821799/ 0911346192
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር