Addis Zemen (Nov 21, 2026)
የተለያዩ የእንጨት ግብዓቶች ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 12/2019
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የእንጨት ግብዓቶች ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ ውስጥ ውል ፈፅሞ ለማሰራት በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1 ሞራሌ እና ፕሌይ ውድ (Phywood) ፣
- ሎት 2፡የተለያዩ መጠን ያላቸው አጠናዎች በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1፡ 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ) ብር ለሎት 2፡ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በድርጅታችን የግንባታ ሳይቶች ወይም ማዕከላዊ መጋዘን ድረስ ማጓጓዝ ይኖርበታል።
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0912744923
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት