Addis Zemen (Nov 22, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለሚገኘው ለየለን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ፦
- ሎት 1 የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፤
- ሎት 2.የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፤
- ሎት 3.የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
- ሎት 4.ህትመት፤
- ሎት 5.የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ ብትን ጨርቅ፤
- ሎት 6.የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው።
3.የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4.ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5.የእቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በየለን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዢ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 10 ቀን እስከ አስረኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ13/3/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22/3/2019 ዓ.ም ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ናሙና የሚያስፈልጋቸው እቃዎች ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው።
11. የጨረታ መዝጊያውና መክፈቻው ከመንግስት የስራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ ቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል።
12. ተወዳዳሪ ድርጅቱ ያሸነፈበትን እቃዎች በየለን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ክፍል ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ኃላፊነት አለባቸው።
13. ውድድሩ በጥቅል /በሎት ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይችሉም።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0942287817 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ማሳሰቢያ፦ ጨረታውን ስትሞሉ በጥቅል ዋጋ መሆኑን አውቃችሁ በጥንታቱ እንድትሞሉ።
- አድራሻ፦ የለን ጤና ጣቢያ ከሸዋሮቢት ከተማ 10 ኪ.ሚ ገባ ብሎ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት