Addis Zemen (Nov 22, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ጨረታ
ቁጥር ተሬ ጤ/አ/ጣ/ኃ/ 085/19ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 3. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤
- ሎት 4. የተለያዩ ብትን የደንብ ልብስ፣ የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማዎች፣
- ሎት 5 ህትመት እና
- ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ በዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸዉ።
3. የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. የእቃዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመከፈል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስታና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማሰያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዢ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ አስረኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከ13/3/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22/03 /2019ዓ.ም ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታዉ በ10ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰአት ላይ ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ማለትም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ይከፈታል።
10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ።
11. የጨረታ መዝጊያዉንና መክፈቻዉን ከመንግስት ስራ ቀን ዉጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ ቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይዘጋና ይከፈታል።
12. ተወዳዳሪ ድርጅቱ ያሸነፈበትን እቃዎች በተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ክፍል ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ሃላፊነት አለባቸዉ።
13. ዉድድሩ በጥቅል /በሎት ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይችሉም።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
15. በጨረታዉ መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0961177912 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታዉን ስትሞሉ በጥቅል ዋጋ መሆኑን አዉቃችሁ እንድትሞሉ።
አድራሻ፡- ተሬ ጤና ጣቢያ ከሸዋሮቢት ከተማ 18ኪ. ሜ ገባ ብሎ
በሰ/ሽዋ ዞን በቀወት ወረዳ አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት የተሬ ጤና ጣቢያ