አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዐ01/2019

አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ ምስክር ወረቀት

2. በዘርፉ የተሰማሩበት ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ(Tin) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ።

3. ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ለተጠቀሱት እቃዎች የማይመለስ በሎት ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለበት።

5. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች ከጨረታው መከፈቻ ቀን በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች ዋጋ የተሞላበት ማቅረብ ግዴታ ነው ካልሆነ ግን ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።

6. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች በአጠቃላይ ብር 10,000 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን በአሥራኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ/ግ/ን/አስ/ገ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።

8. አሸናፊ ድርጅት የታዘዙትን የተለያዩ የግንባታ ስራዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት።

9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ 10%ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሎሎች ተያያዥ ጉዳዩች ጋር በተያያዘ 20% የመጨመር የመቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው። በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያ የማያሲዙ ተጫራቾች እሴት የሚጨምሩ (አምራች ሲሆኑ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል በሚያመጡት ደብዳቤ ይስተናገዳሉ። አድራሻ፡- በጉለሌ ክ/ከተማ ቀጨኔ በድሮ ወረዳ 5 ባሁኑ ወረዳ 4 ከፍ ብሎ ቀበሌ 07/7 መዝናኛ ክበብ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡- 0111568312 ይደውሉ

አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *