የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ አማካሪ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 22, 2026)

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-አፕድ 015/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ አማካሪ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

ስለሆነም፡-ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ።

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት፣ የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በአቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚዉል ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸዉ አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸዉ።

4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን 1ኛ ፎቅ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢ.ሜይል procurement@press.et 
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *