የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር እቃ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚ ዕቃዎች (ሎት 01) እና የደንብ ልብስ ዕቃዎች (ሎት 02) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 003/2019

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር እቃ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚ ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት 01/ የቋሚ እቃዎች
  2. ሎት 02/ የደንብ ልብስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመረቱ እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ (cpo)በማስያዝ ይሆናል። ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
  • የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ከ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 ( ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች አንድ አይነትና ተመሳሳይ የሆነ ማቅረብ አለባቸው።
  • ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።
  • ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም፡- ሎት 01/ የቋሚ እቃዎች የሚሆን 26,000 ( ሀያ ስድስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሎት 02/ የደንብ ልብስ ዕቃዎች የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው።
  • ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
  • መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ፣ ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ 19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ
  • ስልክ ቁጥር፡- 011-1-23-43-69 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *