Addis Zemen (Nov 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 004/2019
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 01 የሠራተኛ ካፌ መስተንግዶ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመረቱ እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ (cpo) በማስያዝ ይሆናል። ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የ ተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ከ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 250 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ። የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።
- ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም። መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ
- ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ሎት 01 የካፌ መስተንግዶ የሚሆን ብር 20,852.00 (ሀያ ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ሁለት ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
- መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ 19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት