Addis Zemen (Nov 24, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2019 ፣
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የወጣቶችና ስፖርት ምክር ቤት በወረዳ 10 ብሪሞ ሜዳ የሚገኘውን G+1 እና G+2 ፣ ለንግድ ቤት የሚሆን የተለያዩ ሱቆች፣ ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል፡
- የቢሪሞ ሜዳ ሱቅ ቁጥር 1 ብዛት 3 ፣የቢሪሞ ሜዳ ሱቅ ቁ 2. ብዛት 17 እንዲሁም በወረዳ 3 አለሙ ሜዳ ለሱቅ አገልግሎት የሚሆን ብዛት 2 አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል። ቤቶቹ የምድር ቤትና G+1 እና G+2 ያለው አጠቃላይ 22 ሱቆች ሲሆን፣ የተሟላ መጸዳጃ ቤት ውሃና መብራት እንዲሁም ጥበቃ ያለው መሆኑን እናሳውቃለን።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፋ ይጋብዛል።
1. የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን የተገዛበት ወይም የተከፈለበት ገቢ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አብሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር/ መያያዝ/ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺር ብር) “በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት ስም በተሰራ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. የተሞላው ዋጋ በተጫራቾቹ በግልጽ ጽሁፍ መቀመጥ እና መፈረም አለበት።
6. ለመለየት ግልጽ ያልሆኑ ጽሁፍ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
7. አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው ለአንድ/ሱቅ ብቻ ነው። ይህን ተላልፎ የተገኘ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
8. አሸናፊ አካላት ሱቆቹ ለመጠጥና ከመጠጥ ጋር የተያያዙ ንግዶችን ለብረታ ብረት ብየዳ ስራ፣ ለቁማር(ቢቲንግ)፣ ለጫትና ሲጋራ እንዲሁም አካባቢ በድምጽ የሚረብሹ ነገሮች መጠቀም ክልክል ነው።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10.ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ- በልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0118721561/0118721553
E-mail!- lideta.Youthandsportoffice@gmail.com
አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቅርንጫም ጽ/ቤት አጠገብ ወይም በላይ ተክሱ ኬክ ቤት አጠገብ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የወጣቶችና ስፖርት ምክር ቤት