Addis Zemen (Nov 23, 2026)
የሰራተኞች ደምብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡ ERT/NCB/G/005/2019
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ለድርጅቱ ሰራተኞች የሚውል የተለያዩ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት፣በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ተቀባይነት ያለው የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) እና በኢትዮጵያ የግዥ ፖርታል (EGP) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ሎት 1 የሰራተኞች ደንብ ልብስ፤ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ናቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለየዘርፉ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ህጋዊ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ለ90 (ዘጠና) ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
4. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀን እና በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ብር በመክፈል በአቃቂ ቃሊቲ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ዲፓርትመንት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከናወናል።
6. የእያንዳንዱ የሎት እቃ ዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ ውስጥ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ለእያንዳንዱ
እቃ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፡
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት – 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ 2፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት
አድራሻ፡-
- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት