Addis Zemen (Nov 23, 2026)
ለመጀመርያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ፡– ሲ/መ/ባ/0010/2019
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለተለያዩ መኪናዎችና ማሽነሪች መለዋወጫ ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ዕቃ አይነት መለዋወጫ |
|
1 |
ማሽነር ሎት መለዋወጫ ሎት1 |
|
2 |
ከባድ መኪና መለዋወጫ ሎት 2 |
|
3 |
ቀላል መኪና መለዋወጫ ሎት 3 |
በዚሁ መሠረት
- ለመለዋወጫ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊከት የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም PPA List እና EGP portal ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዘጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ -5 ቀርበው መግዛት ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ዋስትና (unconditional Bid bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በተጫራቾች የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚቀርቡትን የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid security)፤ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል ) )እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማዕተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣንግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያው ከተክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
- ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡– 046 212-446
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ