የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የግብርና ኬሚካሎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 24, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ SSS-AC-03-2026

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ) (Ethiopian Agricultural Businesses Corporation Agricultural Input Supply Sector) ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግብርና ኬሚካሎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ (NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚገዙ የግብርና ኬሚካሎች ዝርዝር (Lots)፡

  • ምድብ 1 (Lot 1)፡ የአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች (Herbicides)
  • ምድብ 2 (Lot 2)፡ የተባይ ማጥፊያ ኬሚካሎች (Insecticides)
  • ምድብ 3 (Lot 3)፡ የፈንገስ/በሽታ ማጥፊያ ኬሚካሎች (Fungicides)

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 3000.00 ( ሶስት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ እስከ ታኅሣሥ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ዕለት ታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ዋና አዳራሽ ይከፈታል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-
ቃሊቲ የባቡር መጨረሻ በአዋሽ ባንክ መግቢያ ወረድ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና
ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ባለው ሕንፃ ምድር ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት
ትችላላችሁ።
Email: aweln@Ethioagri.com 
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *