በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፎገራ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የመኪና ጎማ፣ አፍሬዲየም ፓምፕ እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 23, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፎገራ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ ግዥች ማለትም 

  • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
    ሎት 3. የመኪና ጎማ፣
  • ሎት 4. አፍሬዲየም ፓምፕ፣
  • ሎት 5. የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ካርድ ያላቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ ብር 500‚000(አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት በፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆንና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ 50,000(አምሳ ሽህ ብር)፣ ለሎት 2. ለኤሌክትሮኒክስ እቃ 40,000(አርባ ሽህ ብር)፣ ለሎት 3. የመኪና ጎማ 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር)፣ ለሎት 4. አፍሬዴም ፓምፕ 40,000(አርባ ሽህ ብር)፣ ሎት 5. ለንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ቁሳቁስ 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. በ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  8. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፉት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  10. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  11. አሸናፊው በውሉ መሠረት ካላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  13.  ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
  14. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት