Be'kur (Nov 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ በደ/ታቦር ከተማ አስተዳደር ላሉት ተቋማት
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የጽዳት እቃ፣
- ሎት 3. የመኪና እቃ (ስፔርፓርት)
- ሎት 4. የመኪና ዘይትና ጥርሳ ጥርስ ቅባት፣
- ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋ።
፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ/ቲን/ቁጥር ያላቸው።
- የግብር ክሊራንስ የከፈለ መሆኑን ማቅረብ አለበት።
- ያቀረበው ዋጋ ከ500,000(አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ብር ማስያዝ አለባቸዉ ሆኖም ማስያዝ ያለባቸዉ የዋስትና አይነቶች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) እና ከታወቀ ባንክ የሚሠጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ሆኖ ከተዘረዘሩት በተጫራቾች ምርጫ በአንዱ ማስያዝ የሚችል ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናል ሰነድ ስርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለጽ ለደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል።
- በጋዜጣ የወጣው ጨረታ የሚከፈትበት እለት በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ስዓቱን ጠብቆ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው ሆኖም የአንዱ ዋጋ ተሞልቶ ጠቅላላዉን ዋጋ ካልተሞላ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይችልም።
- የጨረታ መዝገጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንድም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡።
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደ/ታ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ድረስ ይሆናል ።
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/
መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441
02 09/058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ታቦር ከ/አስ/ገን መምሪያ