Addis Zemen (Nov 25, 2026)
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተር ፕራይዝ ለሆቴል አገልግሎት የሚሆን የተለያዬ የምግብ ግብዓቶችን
ለመግዛት ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለሆቴል ሥራ አገልግሎት የሚሆን የባልትና ውጤቶች፣ እህልና ጥራጥሬ፣ የታሸጉ ምግቦች እና ሌሎች ተዛማጅ ግብዓቶች እና አትክልትና ፍራፍሬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች/ ግለሰቦች ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስዋና ግቢ፣ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ላይ ከሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለሁሉም ሎት የጨረታውን ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሠነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸወል፡፡
6. የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስተኛ ቀን ጠዋት 3፡30 ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ጨረታ ሳጥን ውስጥ ካስገቡ በኋላ በዚያው ዕለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለጽ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም፡፡
8. የጨረታ ውድድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ የግዥ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል፡፡
9. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና ጽ/ቤት፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ
– ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0924388128/0916515716/0993917804 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ