የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ግብዓት የሚያገለግል 15,230 ሜ.ኩ የአሸዋ ምርት ግዥ (የአንድ ሜ.ኩ ነጠላ ዋጋ ብር 9,605.18 ትራንስፖርትና ተ.እ.ታን ጨምሮ) በቁርጥ ዋጋ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 25, 2026)

የአሽዋ ምርት የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ግብዓት የሚያገለግል አሸዋ ምርት ግዥ በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አሸዋ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የምርት አይነት

መለኪያ

ብዛት

የአንድ ሜትር ኩብ ነጠላ ዋጋ ትራንስፖርትን ተ.እ.ታን ጨምሮ በብር

1

የአሸዋ ምርት

ሜ.ኩ

15,230

9,605.18

  1. አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡበት ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ አሸዋ ለማምረት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ወይም በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ አሽዋ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ /ማህበር የተሰጠ ህጋዊ በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት የተረጋገጠ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. በእያንዳንዱ ገልባጭ መኪና የሚያቀርበው ምርት በባለስልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት |Specification/ መሰረት መሆኑ መ/ቤቱ በፈለገው መጠን ላይ የላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል፡፡
  4. በቀን ሊያቀርበው የሚገባው ዝቅተኛ የአሸዋ መጠን 150 ሜ.ኩ በባለስልጣን መ/ቤቱ ሪቨንቲ የሲሚንቶ ማምረቻ ፕሮጀክት አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. በባለስልጣን መ/ቤቱ በመንግስት ውሳኔ የነዳጅ ጭማሪ በሃገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በ5% ሲጨምር ወይም ሲቀንስ የመጓጓዣ አገልግሎት ብቻ በውሉ ላይ በሚገለጸው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል፡፡ የነዳጅ ማሻሻያ ስሌት የማምረቻ እርቀት በተመለከተ የድርጅቱ ትክክለኛ ማምረቻ ቦታ ከአደዋ ዜሮ ዜሮ አደባባይ መነሻ የሚወሰድ ሲሆን የነዳጅ ፍጆታ በ ኪ.ሜ 1.17 ሊትር የሚሰላ ይሆናል፡፡
  6.  አቅራቢዉ አሸዋ ለማቅረብ የሚጠቀምበት ተሽከርካሪ ዝቅተኛ የመጫን አቅም ≥16 ሜ.ኩ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የባለስልጣን መ/ቤቱ በተለያየ ምክንያት የግብአት ምርት አቅርቦት መቀበል ካልቻለ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውል ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
  8. አቅራቢዎች በአቅርቦት ወቅት አሸዋውን ለሚጭኑ ተሽከርካሪዎች በራሳቸው ወጪ ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) በማስገጠም ማቅረብ አለባቸው፡፡ የቁጥጥር ሂደቱም በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል የሚፈጸም ሆኖ የቁጥጥር እና የክትትል ሂደቱ ለማከናወን አቅራቢው አስፈላጊውን የጂፒኤስ (GPS) user account ውሉን ለሚያስተዳድረው ክፍል የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡
  9.  አቅራቢው ውል ከፈረመ በኋላ ባሉት ተከታታይ 3 ቀናት ውስጥ አቅርቦት መጀመር አለባቸው፡፡
  10. አቅራቢዎች ውል ለተዋዋሉበት የውል መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ከታወቀ ባንክ የክፍያ መዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 022 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-15/011-8-71-41-03

አድራሻ:- ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *