ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ዊንዶውስ 11 ፕሮ፣ ዊንዶውስ 10 ፕሮ፡ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ኤል.ቲ.ኤስ.ሲ ፕሮፌሽናል፣ ፒችትሪ አካውንቲንግ ወዘተ ፍቃድ ያላቸው ሶፍትዌሮችን ለማስገጠም ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 26, 2026)

የጨረታ ቁጥር 008/2019 ዓ.ም

ድርጅታችን ዊንዶውስ 11 ፕሮ፣ ዊንዶውስ 10 ፕሮ፡ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ኤል.ቲ.ኤስ.ሲ ፕሮፌሽናል፣ ፒችትሪ አካውንቲንግ ወዘተ ፍቃድ ያላቸው ሶፍትዌሮችን ለማስገጠም ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች –

1. የታደሰ ፍቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤

2. ቫትን አካቶ የማይመለስ ብር 500.00 /ብር አምስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 308 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኰፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኰፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባችኋል፤

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በሲፒኦ ለብቻው በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤

5. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

ፖ.ሣ.ቁ. 3516 ስልክ 011 369 0563 ፋክስ 011 551 3299

አዲስ አበባ፡

ኢትዮጵያ፡፡

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *