Addis Zemen (Nov 26, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር AAPUC 001/19
በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም በአመቱ በተለያየ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚያስፈልጉ እቃዎች ግዢ እና ጥገና፦
- ሎት 1. የዳቦ ማሽን 80X100 የሆነ የጣሊያን ስሪት በኤሌክትሪክ የሚሰራ አጠቃላይ ሰርቪስ ስራ ፤
- ሎት 2. የዳቦ ፓትራ /Flat Aluminum Tray 80cmX100cm X 3cm, Thickness 1.0 / እና የጋሪ ጎማ ግዥ Trolley Wheel Aluminum Cast 10cm Ø/
- ሎት 3 የተለያዩ ቋሚና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 4.ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት 5. የስጋ መፍጫ ማሽን
- ሎት 6.የሰልጣኞች መሮጫ ሸራ ጫማ ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም በዚህ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልፅ ጨረታ ስነ–ስርዓት መሰረት ይፈጸማል፤ ጨረታው የሚያከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2019 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ / Tax clearance / ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም ተ.እ.ታ / VAT / ሰርተፊኬት እና ቲን / TIN / ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፤ በሁሉም ሎቶች ላይ የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ሰነድ በአጠቃላይ የታደሰ መሆን አለበት።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዩጵያ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 28 በስራ ቀናት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ከፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል። ከአደራጃቸው አካል በሚጫረቱበት ሎት በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚገልፅ የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች በሎት 1 ብር 10.000.00 / አስር ሺህ ብር/፤ በሎት 2. ብር 5.000.00 / አምስት ሺህ ብር /፤ በሎት 3. ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/፣ በሎት 4. ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር /፣ በሎት 5. ብር 5.000.00 / አምስት ሺህ ብር/ እና በሎት 6 ብር 5,000.00 / የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ፋይናንስና ግዥ መምሪያ በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሁለት ፖስታ ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጂናል እንዲሁም በሁለት ፖስታ ቴክኒካል ኮፒና ኦሪጂናል በድምሩ በ4 ፖስታ ሰነዶችን በመለየት ማስገባት አለባቸው።
- ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፖሊስ አካዳሚው አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ሳይሆን ቀርቶ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል።
- ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን እንደ የመልካም ስራ አፈፃፀም እና የመሳሰሉትን ማቅረብ የተሻለ ውጤት አለው፤
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኣድራሻ፡– ኮልፌ ሉኳንዳ በሚገኘዉ አዲስ አበባ ፖሊስ ዩንቨርሲቲኮሌጅ ማሰልጠኛ ማዕከል / የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ / አጠገብ።
ለበለጠ መረጃ 011 273-9486 ፤ 011 273-9548 ወይም 251-11 833-3845
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ