ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 05 (ፒያሳ ደጃች ውቤ አካባቢ) ላስገነባው 1/2B+2B+2B+G+9 ድብልቅ አገልግሎት ሕንጻ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የከርሰ ምድር ውሃ ማምረቻ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ ግንባታ፣ ልማት (ዲቨሎፕመንት)፣ የውሃ መሳብ (ፓምፒንግ) ሙከራዎች እና የውሃ ጥራት ምርመራ ስራ ብቁ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 26, 2026)

በድጋሚ የወጣ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ የጨረታ መለያ ቁጥር TSI/PPAGPW/010/2026

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 05 (ፒያሳ ደጃች ውቤ አካባቢ) ላስገነባው 1/2B+2B+2B+G+9 ድብልቅ አገልግሎት ሕንጻ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የከርሰ ምድር ውሃ ማምረቻ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ ግንባታ፣ ልማት (ዲቨሎፕመንት)፣ የውሃ መሳብ (ፓምፒንግ) ሙከራዎች እና የውሃ ጥራት ምርመራ ስራ ብቁ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. የተጫራቾች ብቃት እና ተፈላጊ ሰነዶች

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች እና ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

  • በዘርፉ (የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ / የውሃ ስራ ተቋራጭነት) የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ማስረጃ፣ የዘመኑን ግብር በአግባቡ ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ የታክስ ክሊራንስ ፣
  • በከርሰ ምድር ውሃ ማምረቻ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ልማት ስራ በቂ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ የስራ ልምድ ማስረጃ (የመልካም ስራ አፈጻጸም ወይም የውል ቅጂ)፣
  • በቂ የቁፋሮ ማሽነሪዎች (Rig)፣ መሳሪያዎች እና ብቁ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንዳሏቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣

2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና አከፋፈል

  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የስራ መግለጫ እና ሰነድ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ከሰዓት 11፡00 በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)

ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ስም ተሰርቶ ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

4. የጨረታ ማስረከቢያ እና መክፈቻ ጊዜ

  • የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት።
  • የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት 4ተኛ ፎቅ በኩባንያው አዳራሽ ይከፈታል።
  • ከተጠቀሰው ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

5. ተጨማሪ መረጃ

  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር Tel-011-111-9770/71 or 011-111-9827 ይደውሉ።

የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *