በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ሃራጅ ጨረታ ቁጥር ሃ-20/2018 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ  ስለመሆኑ: ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ

.

የእቃው አይነት

የጨረታዉ አይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ሰዓት

ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

 

1

የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች

ሃራጅ

29/09/2018

 

04/10/2018

 

4:00

 

8:00

 

022 111 8429/  022 211 8925

5. በሃራጅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረታዉ ተሳትፈዉ ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

6. በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም

  • ለምድብ 01,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 331,200.00
  • ለምድብ 02,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 28,000.00
  • ለምድብ 3 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 193,700.00
  • ለምድብ 04 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 768,400.00
  • ለምድብ 05 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 539,000.00
  • ለምድብ 06 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 1,406,400.00
  • ለምድብ 07,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 934,000.00
  • ለምድብ 8,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 781,500.00
  • ለምድብ 09, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 3,700.00
  • ለምድብ ለምድብ 10 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 129,400.00
  •  ለምድብ 11,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 186,500.00
  • ለምድብ12 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 684,000.00
  •  ለምድብ 13 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 39,200.00
  • ለምድብ 14 ተሽከርካሪመለዋወጫዎች ብር 102,700.00 እና
  • ለምድብ 15,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 618,700.00 (Customs commission Adama Branch)

ስም ብቻ .. በማሰራት ያሰሩትንም ... በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

7. በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ /ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስድስተኛው ቀን በኦክሽን መተግበሪያ ላይ በተሰጠው ስዓት መሰረት ጨረታው ይካሄዳል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

12. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ // ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *