Yedebub Nigat (Jun 06, 2026)
14ኛ ዙር የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ለመኖርያና ለቢዝነስ ማዕከልነት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።
ስለሆነም፦
1. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በግንባር በመቅረብና የማይመለስ ብር 900 /ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥመውሰድ ይችላሉ። የሰነድ ሽያጩ እስከ አስረኛው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 9.00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከናወናል።
2. ተጫራቾች ቦታውን በሊዝ ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ፣ የሚጫረቱበትን ቦታ መለያ ቁጥር ኮድ)፣ የቦታውን ስፋትና የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ በጨረታው ሰነድ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናው መጠን፣ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ ሆኖ ከህጋዊ ባንክ በስሙ የተሰራና ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የባንከ አካውንት ቁጥር 1000029392227 እንዲከፈል የታዘዘ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ከመልስ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ አስረኛው የስራ ቀን 10፡55 ሰዓት ድረስ ሀላባ ከተማ ማዘጋጃ ቤቱ ቢሮ ዘንድ በግንባር በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስመዝግቦ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ በሚኖረው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በማዘጋጃ ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቻቾ ካልተገኙ ጨረታው የሚከናወን ይሆናል።
4 የጨረታ አሸናፊዎች ውጤቱ በተገለፀላቸው መሰረት በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በማዘጋጃ ቤቱ በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋቅድመ ከፍያ በመከፈል ውል መፈጸም ያለበት ሲሆን ይህን ካልፈፀመ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይፃፍበታል፤ማስጠንቀቂያው ከደረሰው በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውሉን ሳይዋዋል ከቀረ አሸናፊ መሆኑ ይሰረዛል፣ ለጨረታ ማስከበሪያ አስይዞት የነበረውም ገንዘብ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ ይሆናል።
5 አንደኛ የወጣው ተጫራች ውል ካልፈፀመ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች አንደኛ የወጣው ባሸነፈበት ዋጋ ለመውሰድ ከፈለገበአስር የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችንአሟልቶ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ከፍሎ ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞበድጋሜ ይወጣል።
6. በመመዘኛዎቹ መሰረት እኩል የወጡ ተጫራቾች ካሉአሸናፊውን የመሬት ጨረታ ኮሚቴው በጨረታ ውጤቱተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋና የገቧቸው ግዴታዎች ተመሳሳይሆነው ከመቶ እኩል ነጥብ ካገኙና ከውድድሩ ተካፋዮችውስጥ ብቸኛ ሴት ተወዳዳሪ ካለች የጨረታው አሸናፊእንድትሆን ይደረጋል፡፡ ከዚህ ውጭ ከሆነ አጠቃላይ አሸናፊው በዕጣ እንዲለይ ይደረጋል።
7. ተጫራቹ ቅድመ ክፍያውን አጠናቅቆ ከከፈለ በኋላ ከማዘጋጃቤቱ ጋር የሊዝ ውል በመፈራረም ፕላኑ በሚፈቅደው መሰረትየግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ መርሃ-ግብር አዘጋጅቶበማቅረብ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬትና ቦታውን ይረከባል።
8. ቦታውን ለመግዛት የሚወዳደሩት ተጫራቾች ቁጥር ከሦስት ማነስ የለበትም፡፡ ሆኖም በጨረታው የተሳተፉት ተወዳዳሪዎች ቁጥር ከተጠቀሰው መጠን በታች ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ እንደገና ማስታወቂያ እንዲወጣበት ይደረጋል።
9. ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው ሲሆን አፈፃፀሙም ጨረታው ከተከናወነ በኋላካለው የስራ ቀን ጀምሮ ይሆናል።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቦታ በአካል ተገኝተው መጎብኘት ወይም በፕላን መልክ መመልከት ከፈለጉ ከጨረታውቀን በፊት በጨረታ ኮሚቴ አስጎብኝነት ቦታውን ማየት ይችላሉ።
11. ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብአይቻልም።
12. በጨረታው ህጋዊ የሆነ የማንኛው ሀገር ዜግነት ያለው መወዳደር ይችላል።
13. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
14. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በአሃዝና በፊደል መግለፅ አለባቸው፡፡ ሆኖም የአሃዝና የፊደል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው የገንዘብ መጠን ገዥ ይሆናል።
15. በጨረታ ኮሚቴ የተሰረዘበት ተጫራች ቅሬታ ካለው በ5 የስራቀናት ውስጥ ለማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ማቅረብ ይችላል፣
16. ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት በመፈፀም ወይም የጨረታውን ሂደት ለማዛባት መሞከራቸው ከተረጋገጠ ከጨረታው ይታገዳሉ፣ ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ሳይመለስላቸው ለመንግስት ገቢ ይደረጋል በተጨማሪም በዓመቱ በሚካሄዱ ጨረታዎችም እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
17. የጨረታ ውጤት በከተማ ከንቲባ ኮሚቴው ከፀደቀ በኋላጨረታው በተከፈተ ሰባት የስራ ቀናት ውስጥ በማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ሊዝ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደቡብ ንጋት ጋዜጣ ይወጣል።
18. ተጨማሪ ዝርዝር ካስፈለገ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-556-00-08/0912122401 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ!
በድህረ-ገፅ www.halabamun.gov.et
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት