የጉራፈርዳ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የኦጀምታ ፍል ውሃን ለማልማት የእንግዳ መቀበያ እና ማረፍያ፣ የወንድ እና የሴቶች ማደሪያ፣ የመረጃ ዴስክ፣ የዘበኛ ቤት እና ሽንት ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉራፈርዳ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የኦጀምታ ፍል ውሃን ለማልማት የእንግዳ መቀበያ እና ማረፍያ፣ የወንድ እና የሴቶች ማደሪያ፣ የመረጃ ዴስክ፣ የዘበኛ ቤት እና ሽንት ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉራፈርዳ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት /ቤት 2018 የበጀት ዓመት ሊያሠራ ላቀደው የኦጀምታ ፍል ውሃን ለማልማት የእንግዳ መቀበያ እና ማረፍያ፣ የወንድ እና የሴቶች ማደሪያ፣ የመረጃ ዴስክ፣ የዘበኛ ቤት እና ሽንት ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. የደረጃቸው 6 / (BC/GC-6) እና ከዚያ በላይ የሆነ፤

2. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የብቃት ማረጋገጫ፣የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት በማቅረብ በወረዳው ///አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 02 የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል።

3. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢ ሁኔታ ማቅረብ የሚችል፣

4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

5. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በሰም በማሸግ እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

6. እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም መምታት፣ ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ጽሑፍ መጻፍ አለበት።

7. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።

8. እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደርበትን የስራ ቦታ፣ የተጫራቹ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግልፅ መፃፍ አለበት።

9. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው የሚታሸገው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ተኛው ቀን በወረዳው ///አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ከጠዋቱ 400 ሰአት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል።

11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ተኛው ቀን በወረዳው ///አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ከሰአት በኋላ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 17 77 16 04 09 10 15 11 28 09 19 33 15 42 እና 09 98 56 50 41 ላይ መደወል ይችላሉ።

የጉራፈርዳ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *