Addis Zemen (Jun 29, 2026)
በ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ሆቴሎች ንግድ
አክሲዮን ማህበር
የአገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር ለአክሲዮን ማህበሩ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ጥናት አገልግሎት የሚሰጡ ብቁ አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ድርጅታዊ መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ማስጠናት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በመስኩ የሙያ ፈቃድ ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ክሊራንስ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ፒያሳ ሞዝቮልድ ሕንፃ ላይ በሚገኘው ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከጨረታ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /Bid Bond/ የሚወዳደሩበትን የሥራ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሺያል ፕሮፖዛል ለየብቻው ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው በወጣ በአሥራ አንደኛው ቀን ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ በአክሲዮን ማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤
- አክሲዮን ማህበሩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0903307777 ወይም 0911392023 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ሆቴሎች
ንግድ አክሲዮን ማህበር