Addis Zemen (Jul 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ነሐሴ 25ቀን 2002ዓ.ም በበጎ አድራጎት ማህበራት ኤጀንሲ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ በቁጥር 2lchs/4/0610ሠ.1971 የተመሰረተ ሀገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ መደበኛ ስራውን የጀመረው ደግሞ ሰኔ 09 ቀን 2003 ዓ.ም ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 90 በኦቲዝም ጥላስር ያሉ ልጆችን በትምህርትና ስልጠና እያገዘ ይገኛል፡፡ ድርጅታችን የ2018ዓ.ም በጀት እውቅና ያለው ኦዲተር አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በግልፅ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ. የሞያ ማረጋገጫ ያለው
ለ. ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
ሐ. ለዘመኑ ግብር ስለመክፈሉ መረጃ ማቅረብ ሚችል መሆኑ
መ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ
ሠ. ከፌዴራል ወይም ክልል ኦዲተር መስሪያ ቤት ለበጀት አመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው
ተጫራጮች የውድድር ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ድርጅታችን ቢሮ ድረስ በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡– ቄራ ልዩ ስሙ አልማዝዬ ሜዳ ገባ ብሎ ወይም ሰዲል ት/ቤት ፊትለፊት
ስልክ ፡– 0911 047 859 / 0998 834 957
ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል