የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተገነቡ የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ማለትም የተርሚናል፣ መጠለያ፣ ሽንት ቤቶችን እና ለህዝብ ትራንስፖርት መጠበቂያ ሼድ የጽዳትና ደህንነት አገልግሎት ግዥ በመፈጸም በ3ኛ ወገን ለማሰራት ስለፈለገ አገልግሎቱን መስጠት ከሚችሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተገነቡ የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ማለትም የተርሚናል፣ መጠለያ፣ ሽንት ቤቶችን እና ለህዝብ ትራንስፖርት መጠበቂያ ሼድ የጽዳትና ደህንነት አገልግሎት ግዥ በመፈጸም በ3ኛ ወገን ለማሰራት ስለፈለገ አገልግሎቱን መስጠት ከሚችሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 10, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2018

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ 2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር ////ግጨ/10/2018 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተገነቡ የትራንስፖርት መሰረተልማት ማለትም የተርሚናል መጠለያ ሽንት ቤቶችን እና ለህዝብ ትራንስፖርት መጠበቂያ ሸድ የጽዳትና ደህንነት አገልግሎት ግዥ በመፈጸም 3 ወገን ለማሰራት ስለፈለገ አገልግሎቱን መስጠት ከሚችሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡

  • የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር) የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ 11ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ሰዓት ይከፈታል፤
  • ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 1100 ሰዓት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈርም አለባቸው።

ማሳሰቢያ፡/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡መገናኛ ስሪ ኤም ሲቲ ሞል ህንፃ 5 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 639-4655/ 011 639-3010 መጠየቅ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *