Addis Zemen (Jul 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
ለ2019 በጀት ዓመት አመታዊ የተሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ አገልግሎት
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው /orignal/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 4//2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እሰከ 15 ኛው ቀን ማለትም 18/11/2018 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 2 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ 4/11/2018 ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም እስከ 19/11/2018 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡01 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል ፡፡
6የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡
6. ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ጨረታውን በሎት የሚያወዳደር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
7. የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሽናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
9. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
03355421119
0335540364
በአብክመ የኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ