Addis Zemen (Jul 11, 2026)
የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ 001/2018 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር፡–ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 001/2018 ዓ.ም
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተለያዩ የአገልግሎት ግዥ ፣ የደንብ ልብስ እና የአቃቤ ህግ የችሎት ልብስ ሱፍ ጨርቅ በገበር የተስፋና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የታሸገ ውሃ ግዥ
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3. የተለያዩ የጉዞ መኪናዎች ኪራይ
- ሎት 4. የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎችና ልዩ ልዩ እቃ
- ሎት 5. የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 6. የደንብ ልብስና የኘሮቶኮል ልብስ
- ሎት 7. የድንኳንና የወንበር ኪራይ
- ሎት 8. የመኪና ጥገና (ሰርቪስ)
- ሎት 9. ዲኮር ስራ ኪራይ
- ሎት 10. የደንብ ልብስ ማሰፊያ
- ሎት 11. ዲጄ እና የሙዚቃ ኪራይ
ስለዚህ በዚህ የስራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
4. የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
5. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. 20,000 ብር ሎት 2. 20,000 ብር ሎት3. 30,000 ብር ሎት4 20,000 ብር ሎት 5. 20,000 ብር ሎት 6. 30,000 ብር ሎት 7. 20.000 ብር ሎት 8.30,000 ብር ሎት 9. 20.000 ብር ሎት 10. 10.000 ብር ሎት 11. 20,000ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር) በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ ፣
7. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11፡30 ይሆናል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
9. ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ህጋዊ ወኪል ለመሆናችሁ የሚገልጽ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡ /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
13. ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
14. በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል ፡፡
15. በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል፡፡
16. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. በበጀት አመቱ መላውን ዓመት የዋጋ ማስተካከያ የማናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
18. የመኪና ኪራይን በተመለከተ ቀንና ለሊት ሰዓት ሳይገድበው ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር፡– 0921 770 036 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡– አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት