የቢራ ሠራተኞች አጠቃላይ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ 12,122.06 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መዋለ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለንግድ ሥራ አገልግሎት እንዲውል በጨረታ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የቢራ ሠራተኞች አጠቃላይ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ 12,122.06 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መዋለ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለንግድ ሥራ አገልግሎት እንዲውል በጨረታ አውጥቷል


Reporter (Aug 19, 2026)

የቢራ ሠራተኞች አጠቃላይ ሥራ አክሲዮን ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቢራሮ 01/2018-12

1. የንብረቱ ዝርዝር መግለጫና አድራሻ

, አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ቦርከና ክፍለ ከተማ።

, ልዩ ቦታው ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር ጎን።

, የመሬት ስፋት 12,122.06 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መዋለ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት።

, የይዞታው የአሁኑ አገልግሎት ለንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውል ይዞታ ነው።

, ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሲሆን ኮምቦልቻ ዋናው መስሪያ ቤት እስከ ቀኑ 900 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።

2. ለተጫራቶች የሚቀርቡ ሕጋዊ መስፈርቶች

, ተጫራቶች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

, በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ) ብቻ ከዋናው መስሪያ ቤት ኮምቦልቻ (ወሎ) መግዛት አለበት::

, የጨረታ ማስከበሪያ (የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1689) ተጫራቶች የወሰዱትን ግደታ ለማረጋገጥ የሚሆንና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 1% ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።

, ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ 3ኛው ቀን ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት ከጧቱ 400 ሰዓት ተጫራቶች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡ ሆኖም ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

3. የአክሲዮን ማህበሩ መብት

, አክሲዮን ማህበሩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ ቁጥር 0912 395 167 / 0970 638 884

(ኮምቦልቻ)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *