Addis Zemen (Aug 21, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚሰሩ ኪሜትር የመንገድ ጥገና ሥራ ህጋዊ በመስኩ የተሰማሩ GC 5 እና RC 5 ደረጃ ያላቸው ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በሰዓት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ::
በዚህ መሠረት ማናቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ከመንገድ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኮንትራክተሮች እንዲሳተፉ እንጋብዛለን::
ተሳታፊዎች፡-
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ የዓመቱን ግብር የከፈሉና ዋናና ቅጂ መረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ::
- ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ _
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰረተ ቼክ CPO 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉ::
- ጠቅላላ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የፌደራል መንግስት የተደነገገውን የግዥ ሕግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው ::
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ ለወደፊትም በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ በሚካሄደው በመንግስት የግዥ ጨረታ አይሳተፉም:: ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም::
- በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ ማሽኖች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ መለወጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መውጣት አይችሉም::
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላይ መግለጫ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት ቀን (5) ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና አድራሻ ማህተም መጥቀስ አለባቸው::
- የጨረታውን ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል::
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት የሰነድ ሽያጭ ይከናወናል::
- የጨረታው ሰነድ አቅራቢ ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛ የስራ ቀን ጠዋት 3:00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ::
- የተሰረዘ የተደለዘ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ክሪላንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ዝርዘር ጠቅላላ መስፈርቶች በጨረታው ሰነድ ላይ ያሉ መሆናቸውን እንገልፃለን::
- የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል እና የቴክኒክ ሰነዶች ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነዶች ለየብቻቸው ታሽገው በተጨማሪም CPO ለብቻው በአንድ ፓስታ በማድረግ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ጥቅል ትልቅ ፓስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ስለጨረታው የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር 0471160012 መደወል ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት