በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 28, 2026)

የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፡ የጽዳት እቃዎች የቋሚ አላቂ እቃዎች፡ ቋሚ እቃዎች፡ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፦

1.ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ከግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት በኦን ላይን የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸው እቃዎችን እንዲሁም የፎቶ ናሙና የሚያፈልጋቸው እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚቻል ሲሆን ለሎት /1/ አላቂ የቢሮ እቃዎች 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ለሎት /2/ ደንብ ልብስ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ለሎት /3/ የጽዳት እቃዎች 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት /4/ ቋሚ እቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ለሎት /5/የቋሚ አላቂ እቃዎች 10,000/አስር ሺህ ብር/ ለሎት /6/የአገልግሎት ግዥ 8,000/ስምንት ሺህ ብር/ሲሆን የሁሉም ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ወጭ ሌላ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘቱ እቃዎችን ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር እያንዳንዱ እቃ ድምር በጨረታ ሰነዱ ላይ በአለው የዋጋ መጠየቂያ ረድፍ በግልጽ ስረዝ ድልዝ ሳይኖር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ በመጠቀም የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾች ጨረታ ውስጥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ።

6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውን የድርጅቱን ሙሉ ስም በየአንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዶችን በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

7. የጨራታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ። ለወደፊቱም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋሉ። የአስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

9. ተጫራቾች ከላይ የተጠየቁትን ማስረጃዎች አሟልተው አሽገው አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው በአስረኛው የስራ ቀን 10፡30 ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በስራ ቀን 4፡30 ላይ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።

12.ጨረታውን ያሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈፀም ይኖርበታል።

13. ተጫራጮች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሱ እቃዎች ዝርዝር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መጫረት ይችላሉ።

14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ለአንድ እቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል በአንድ አይነት ሁለት ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

አድራሻ ፡- ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ብሩክ ክሊኒክ 200 ሜትር ገባ ብሎ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 011 832 9662

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት