Be'kur (Sep 07, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም ፡-
- ሎት 1. የማገዶ እንጨት፣
- ሎት 2. የዳቦ አቅርቦት፣
- ሎት 3. አትክልትና ፍራፍሬ እና
- ሎት 4. የወፍጮ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነበር፣ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድግ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታው ከጳጉሜ 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በጋዜጣ ላይ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ማለትም መስከረም 07/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ወይም ኮሬክሽ ፍሉድ መጠቀም አይፈቀድም፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃዉን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ እንዲሁም የወፍጮ አገልግሎት የሚሰጡ ደግሞ የትራንስፖርት እና የጫኝ አውራጅን ወጭ ታሳቢ በማድረግ የሚወዳደር ሲሆን በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት