የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 በጀት የተለያዩ ግዥዎችን ማግኘት እና መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 በጀት የተለያዩ ግዥዎችን ማግኘት እና መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 07, 2026)

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 በጀት የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም

  •  ሎት 1. ለራተኞቹ ጥዋት እና ማታ የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ኪራይ፣
  • ሎት 2. የኦዲት አገልግሎት ከ2016 እስከ 2017 የ2 ዓመት እና
  • ሎት 3. የመኪና እስፔር ፓርት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡

 በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ለሎት 2 የመ/ቤቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የታደሰ የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6.  የሎት 2 ተጫራቾች የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በተለያየ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከኦርጅናል ወይም ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የሰርቪስ መኪናው ኪራይ የዓመቱን ሂሳብ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8.  ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  9. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  10. ሎት 1 ለኪራይ የቀረበውን ተሸከርካሪ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፣ በየወሩ የአገልግሎት ክፍያው ሲፈፀም ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ ፣ሞዴላቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2011 እና በላይ ያለና የወንበር ልብሱ የተሻለ ከአባይ ማዶ ለሚመጡ ሰራተኞች 44 ወንበር እና ከዚያ በላይ የመያዝ አቅም ያለው እና የሚንቀሳቀሱበት ፌርማታ (ቦታዎች) በጨረታ መመሪያው የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  11. ሎት 2 የሂሳብ ምርመራውን (ኦዲቱን) በባሕር ዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዋናው ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም ከድርጅታችን ንብረት ክፍል ድረስ እቃውን በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  13.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14.  ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 20 50 79 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *