የሽመልስ ሁብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሽመልስ ሁብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 08, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር፡ 01/2018

የሽመልስ ሁብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን

  • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብሶች ፣
  • ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች
  • ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 6 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 7 የተማሪዎች አጋዥ መፅሐፍት፣
  • ሎት 8 የኤሌትሪክ ዕቃዎች የህንፃ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 9 የሰራተኞች ባጅ እና መታወቂያ በግልፅ ጨረታ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች፡-

1. በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃዎችን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣ የሚችሉ፣

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የዕቃ ዓይነቶች በተናጥል የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን CPO ኦርጅናል ሰነድ የታሸገበት ኤንቬሎፕ ውስጥ መካተት ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዕቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው በተጠቀሰው መጠየቂያ መሠረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራጮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 /አንድ/ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጥበትን ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ በመሙላት እና ሌሎች ማስረጃዎችን በማህተም በማረጋገጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10 የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት በታሸገው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

8. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ከ7ኛው ከሰባተኛው/ ቀን ቀጥሎ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ አለበት፣

9. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

አድራሻ ፡- ገነት ሆቴል ጀርባ

በእዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቂርቆስ

ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት