በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ህብረተሰብ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበውን ስኳር በዩኒየናችን በኩል ለማጓጓዝ ለአንድ አመት በአንድ ዙር 800 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ህብረተሰብ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበውን ስኳር በዩኒየናችን በኩል ለማጓጓዝ ለአንድ አመት በአንድ ዙር 800 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል


Be'kur (Sep 07, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ህብረተሰብ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበውን ስኳር በዩኒየናችን በኩል ለማጓጓዝ ለአንድ አመት በአንድ ዙር 800 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች የደረቅ ጭነት ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የኦፕሬተር ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብና ማያያዝ የሚችሉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን በግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት እና ክብ ማህተም በማድረግ በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግና አለባቸው፡፡
  4.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  6.  በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪዥን መውስድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  9.  አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትእዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም (ሲፒኦ) የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስገባትና ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  10.  ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11.  በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12.  ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 10 32 /640 /09 00 31 89 07 በመደወል መረጃ በመጠየቅ እና መረዳት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *