Addis Zemen (Sep 09, 2026)
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር 5000 ኬ.ጂ መጫን የሚችል ፎርክ ሊፍት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ በዚህም እለት የቴከካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን ቴክኒካል መስፈርቱን ያለፉ ተጫራቾች ብቻ በቀጣይ ጊዜ ፋይናንስ ለመክፈት የሚጠሩ ይሆናሉ፡፡
6. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር 01115 15 50 05 / 0115 51 88 72
ፋክስ 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር