Addis Zemen (Sep 10, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ.ብ.ክ.መ. ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በUNDPና መደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ፣
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪዎች ፤
- ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፤
- ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣
- ሎት4 የባጃጅ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ሎት 5 የሞተር ሣይክል ዕቃዎች፣
- ሎት 6 የእንስሳት መድኃኒቶች ፣
- ሎት 7 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣
- ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤
- ሎት 9 ፈርኒቸር እቃ፣
- ሎት 10 የመኪና ባትሪና ጎማ እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት –
- በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታስክ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የኤክሳይዝ ታከስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- የበጀት አመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፤
- ዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥው መጠን ብር 200,000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሠነዶች ግልፅና የሚነበቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 የጽህፈት መሣሪዎች ብር 31,531፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ብር 5000፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 25000፣ ሎት 4 የባጃጅ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 6000፤ ሎት 5 የሞተር ሣይከል ዕቃዎች ብር 4000፣ ሎት 6 የእንስሣት መድኃኒቶች 7000፣ ሎት 7 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 3000፤ ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 2000፣ ሎት 9 ፈርኒቸር እቃ ብር 8000፣ ሎት10 የመኪና ባትሪና ጎማ እቃ ብር 15000፤ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ፣(CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል ) ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይፈፀማል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን፣ በጨረታ ሠነዱ የሠጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም ::
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚቀርቡ ዕቃዎችን ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጐ ይወስዳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 01-62 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን