ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የIT እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የIT እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Sep 09, 2026)

የተያዩ IT እቃዎች ድጋሚ የወጣ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ HBSCITEQUIPMENT/01/0001/26

የተለያዩ IT እቃዎች ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ IT እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣

3. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው

4. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 29ኛው ቀን 1100 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በአካዉንት ቁጥር 1000004335299 በመክፈል የገባበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፤

5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ

) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሽግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት፤

) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በማሽግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ /ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 29ኛው ቀን 1100 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

6. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሐበሻ ቢራ . ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።

7. ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል

8. የጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ምንረከበው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ሆኖ 30ኛው ቀን ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *